Rules and Regulations

“Excellence in Everything”

Students should behave according to the following guidelines at all times

ቢ.ሲ.አይ አካዳሚ የቤተልሔም ካምፓስ የተማሪዎች የመተዳደሪያ ደንብ

  1. የተማሪው መብት
    • ማንኛዉም ተማሪ የመማር መብት አለዉ፡፡
    • ያልገባዉን የመጠየቅ አና የማወቅ መብት አለዉ፡፡
    • በክበባት የመሳተፍ መብት አለዉ፡፡
    • ተማሪዎች ከት/ቤቱ አስተዳደር ከመምህራን እና ከወላቻቸዉ ጋር አስፈላጊዉን ድጋፍ አና እገዛ የማግኘት መብት አላቸዉ፡፡
    • ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸዉን በሚጠቅሙ ስራዎች በአካባቢያቸዉ ልማት የመሳተፍ መብት አላቸዉ፡፡
    • የጥናት ጊዜያቸዉን በአግባቡ የመጠቀም መብት አላቸዉ፡፡
  2. የተማሪው ግዴታ

2.1 ማንናዉም ተማሪ በስዐቱ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ መገኘት ግዴታ አለበት፡፡

2.2. ማንኛዉም ተማሪ የሰንደቃላማ መዝሙር በመዘመር ስርዓቱ አሰኪያበቃ በተጠንቀቅ ቆሞ ማክበር ግዴታ አለበት፡፡

2.3. ማንኛዉም ተማሪ ከት/ቤቱ በህመምም ሆነ በተለያየ ምክንያት ቢቀር ለክፍል ሀላፊ መምህሩ በስልክ ወይም በአካል ቤተሰብ መቶ ማስፈቀድ አለበት፡፡ ሆኖም ግን ያለ ፊቃድ የቀረ ተማሪ ከወላጅ ጋር በመምጣት ለክፍል ሀላፊዉ መምህር  ምክንያቱን ሳያስረዳ ክፍል ገብቶ መማር አይችልም፡፡ ታሞም ከሆን የቀረበትን የሃኪም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

2.4. ለትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ እንደ ደብተር እስከርቢቶ እርሳስ ላጲስ የእስፖርት ልብስ እና ላፕቶፕ ወይም ታብሌት PC የመሳሰሉትን አሟዋልቶ መገኘት የኖርበታል፡፡

2.5. በት/ቤት ዉስጥ በሚቋቋሙ ክበባት ቢያንስ በአንድ ክበብ የመሳተፍ ግዴታ አለበት፡፡

2.6. ተማሪዎች መምህራኖቻቸዉ እና የት/ት ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞችን ማክበር አና መታዘዝ ይኖርባቸዋል፡፡

2.7.ስለታማ ነገሮችን ፣ ጉዳት ሊያሰከትሉ የሚችሉ ነገሮችን እንዲሁም ለሱስ አጋላጭ የሆኑ ነገሮችን በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ዉሰጥ ይዞ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ ከመሆኑም በላይ እነዚህን ነገሮች ይዞ የተገኘ ተማሪ የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድበት ይደረጋል፡፡

2.8. የትምህርት ቤቱን ንብረት የመጠበቅ እና የመንከባክብ ግዴታ አለበት፡፡

2.9. ማንኛዉም ተማሪ የቤት ስራዎችን የክፍል ስራዎችን በመምህራን የሚታዘዙ ስራዎችን ሰርቶ መገኘት አለበት፡፡

2.10. በት/ቤት ቅጥር ግቢም ሆነ ከቅጥር ግቢ ዉጪ ቁማር መጫወት መደባደብ አና ሌሎች አላስፈላጊ ባህሪያትን ማሳየት እና መፈፀም ፈፅሞ የተከለከለ ነዉ፡፡

2.11. ማነኛዉም ተማሪ በትምህርት ሰዐት ከክፍል ዉጪ መገኘት የለበትም፡፡

2.12. ተማሪዎች በት/ት ቤታቸዉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአካባቢያቸዉ በሚገኙ የልማት ስራዎች የመሳተፍ ግዴታ አለባቸዉ፡፡

2.13. የት/ት ቤቱ ተማሪዎች ከክፍል ጓደኛቸዉ እና ከት/ቤቱ ተማሪዎች ጋር መልካም የሆነ ግንኑነት መፍጠር ይኖርባቸዋል፡፡

2.14. ማንኛዉም ተማሪ ለት/ቤቱ ደንብ እና ስርዐት ተገዢ መሆን አለበት፡፡

2.15. ወንድ ተማሪዎች  ፀጉራቸዉን ባጭሩ መስተካክል፤ የት/ቤቱን ደንብ ልብስ ት/ቤቱ በሚያዘዉ የልብስ ስፌት ስርዐት መሰረት ያልተቀደደ ዩኒፎርም የመልበስ ግዴታ አለባቸዉ፡፡

2.16. ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸዉን ከማንኛዉም ቀለም ወይም ሂና ነፃ የሆነ ወደታች ተጎንጉኖ፣ ተሰርቶ የመምጣት ግዴታ አለባቸዉ፡፡

2.17. ማንናዉም ተማሪ ጌጣጌጥ እና ቀለበት፣እግር ላይ ጌጥ ማድረግ፣ ጥፍር ቀለም መቀባት ፣ መኳኳል ፈፅሞ የተከለከለ ነዉ፡፡

2.18. ማንኛዉም ተማሪ ት/ቤት ዉሰጥ ሞባይል ይዞ መገኘት የለበትም፡፡ በሆነ አጋጣሚ ይዞ ቢገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ብር 500 ቅጣት በመክፈል  የተማሪ ወላጆች ሞባይሉን መረከብ የሚችሉ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የተገኘ ተማሪ ግን ብር 1000 በመክፈል ሞባይሉን የት/ት ዘመኑ መጨረሻ  ሰኔ 30 ላይ  ወላጆች እንዲረከቡ ይደረጋል፡፡

2.19. ማንኛዉም ተማሪ የት/ቤቱን መታወቂያ ይዞ የመገኝት በተጠየቀ ጊዜም የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡

2.20. ማነኛዉም ተማሪ በእረፍት ጊዜ በግቢ ዉሰጥ ድንጋይ መወራወር፣ በካራቴ እና ሌሎች አደጋ የሚያደርሱ ጨዋታዎችን እና መራገጥ ለከፍተኛ ጉዳት ስለሚያጋልጥ ከዚሀ ድርጊት መቆጠብ እና መጠንቀቅ የሚኖርባቸዉ ሲሆን ጉዳት ቢደርስ ተጠያቂዎች እራሳቸዉ መሆናቸዉን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

2.21. ማንኛዉም ተማሪ የት/ቤቱን ንብረት መስበር እና ማበላሸት፣ የተለያየ ጉዳት ማድረስ የለበትም፡፡ ይህንን አድርጎ ቢገኝ ያጠፋዉን ንብረት ግምት ከፋይ ሲሆን በተጨማሪ ላደረሰዉ ጥፋት በዲፕሊን ተጠያቂ ይሆናል፡፡

2.22. ማንኛዉም ተማሪ ይዞ ለመጣዉ የት/ት መሳሪያ ፣ዩኒፎርም፣ ሹራብ፣ የምሳ እቃ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡ ይህ ሆኖ ባይገኝ ት/ቤቱ ሃላፊነት አይወስድም፡፡

በክፍል ውሰጥ የሚተገበሩ ተግባሮች

  1. ማንኛዉም ተማሪ መምህሩ ሲያሰተምር እና ሲያስረዳ ማዉራት መቀለድ መሳቅ ከቦታ ቦታ መዘዋወር የለበትም፡፡

2.ማንኛዉም ተማሪ የክፍሉን ንፅህና ማቆሸሽ ፣ ደብተር መቅደድ ከክፍል ዉሰጥ እና ዉጪ ወረቀቶችን መጣል የሌለበት ሲሆን ቆሻሻዎችን በቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል ሃላፊነት አለበት፡፡

  1. ማንናዉም ተማሪ የሚቀመጥበት ወንበር እና ዴስክ ላይ መፃፍ መሞነጫጨር ያልተገባ ነገር መፃፍ አና ማቆሸሽ የሌለበት ሲሆን ይህን አስነዋሪ ድርጊት የሚፈፅም ተማሪ የተበላሸዉን የማፅዳት እንዳስፈላጊነቱም የማሳደስ ወይም በሌላ አዲስ የመቀየር ግዴታ አለበት፡፡
  2. ማንኛዉም ተማሪ የስፖርት ትጥቅ በእስፖርት ሰዐት ለብሶ መገኘት እና መሳተፍ ይኖርበታል፡፡
  3. ማንኛዉም ተማሪ በፈተና ጊዜ በራሱ ተማምኖ መስራት እእጂ ከሌላ ተማሪ በሌላ መንገድ መስራት በጣም ስነ-ምግባር የጎደለዉ በራሱ የማይተማመን ስለሚያደርገዉ ይህንን አይነት ድርጊት ፈፅሞ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
  4. ግዴታቸዉነ በማይወጡ እና የት/ቤቱን ስነ-ስርዐት በማያከብሩ ተማሪዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚከተሉት ይሆናሉ
  • ተማሪዉ በቅድሚያ ጥፋቱን ተረድቶ እንዲፀፀት እድል መስጠት፡፡
  • ጥፋቱን ለወላጆች አሳዉቆ በማረም አንዲተባበሩ ማድረግ፡፡
  • ተግፃፅ ወይም ማስጠንቀቂያ አንዲሰጠዉ ይህም ወላጆችን ጠርቶ በማስፈረም እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በግል ማህደሩ እንዲመዝግብ ማድረግ፡፡
  • የጥፋቱን ከፍተኛነት ወይም የተማሪዉ ተደጋጋሚ ጥፋት መጥፎ አርአያነት ታይቶ ጠባዩ ተስተካክሎ የት/ቤቱ ጤናማ አባል ሊሆን እስኪችል ድረስ ከት/ቤት አንደ ጥፋቱ ክብደት ለአንድ አመት ወይም ለሁለት ዓመት ማግለል፡፡
  • ለፈፀመዉ ጉዳት ወይም ጉድለት በማካካስ አንዲሰተካከል ማድረግ፡፡
  • ተማሪዎች ከነበሩበት ክፍልየፀባይ እና ተያያዥ ጉዳዮች ‘C’ከሆነ በቀጣዩ ዓመት ከት/ት ቤቱ የሚታገዱ ይሆናል;;
  • አንድ ተማሪ በአንድ መንፈቀ አመት 4 ቀናቶችን ወይም በአመት ዉሰጥ አጠቃለይ 8 ቀናቶችን በአርፋጅ ከተመዘገበ በቀጣዩ ዓመት ከት/ት ቤቱ የሚታገድ ይሆናል;;
  • በአንድ የትምህርት መንፈቀ አመት ዉሰጥ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለ15 ቀናት እና ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለ10 ቀናት በት/ት ላይ ካልተገኙ በፈተና ላይ መቀመጥ አይችሉም፡፡

4.ያለምንም ማስጠንቀቂያ ተማሪዎችን ከት/ቤት እንዲሰናበቱ የሚያደርጉ የጥፋት አይነቶች

    • የፈተና ስርቆት አና ሌሎች ተማሪዎች አንዲሰርቁ ማድረግ፡፡
    • በአጥር ሾልኮ የገባ ወይም የወጣ ተማሪ፡፡
    • መምህር እና የት/ት ቤቱን ሰራተኛ የሰደበ 1 ዓመት ፣ለመደባደብ የሞከረ 2 አመት፣ የደበደበ 3 ዓመት ከት/ት ቤቱ ይታገዳል፡፡
    • ሴት ተማሪዎችን የዘለፈ ወይም የሰደበ ይህንን ሁለት ጊዜ የደገመ እና ጥፋቱን ለማረም በተደረገዉ ጥረት ያልታረመ፡፡
    • አንድ ወንድ ተማሪ ሴት ተማሪዎችን ከደበደበ 2 ዓመት፣ ለመደብደብ ከሞከረ 1 አመት ከት/ቤቱ ይወገዳል፡፡
    • ወንድ ተማሪ ከወንድ ተማሪ ጋር፣ ሴት ተማሪ ከሴት ተማሪ ጋር ቢደባደብ/ብትደባደብ 1 አመት ከት/ቤቱ ይታገዳል/ትታገዳለች፡፡
    • ስለታማ ነገሮች፣ አልኮል እና ሱስ የሚያሲዙ አደንዛዠ እፆችን ይዞ ወይም ተጠቅሞ የተገኘ ተማሪ ለ1 አመት ከት/ቤቱ ይታገዳል፡፡
BCI Academy Logo

BCI ACADEMY

BCI ACADEMY

Get in touch!

Located in
3 km from the Bishoftu Education Office on the south side of Zukala to Kajima road.

Latitude: 4'93'297''
Longitude: 9'67'486''

School Contact
Ato Degu Deme 0911065876

BCIACADEMY2016@GMAIL.COM

Scroll to Top